Student Announcement

ደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ከ ቀን 14-22/08/2015 ዓ.ም ድረስ COC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን 09/10/2015 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ እና መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ለሰርትፊኬት ፎቶ ያልሰጣችሁ በእለቱ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባን፡፡

የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የማታና ተከታታይ ፕሮግራም  በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅት አጠናቋል፡፡

ስለዚህ በድጋሜ ምዝገባ 27/07/2015 ጀምሮ ለሦስት ተካታታይ የስራ ቀናት  የሚካሄድ በመሆኑ፡- ትምህርት ፈላጊዎች በደረጃ 1 እስክ ደረጃ አራት በማታ ና ቅዳሜና እሁድ  መርሃ-ግብር በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

  1. የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ውጤት ማስረጃ
  2. 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት
  3. የ 8ኛ ክፍል ውጤት ማስረጃ

የክፍያ ሁኔታ፣  ለንድፈ ሀሳብ በሰዓት  ለደረጃ 1 እና 2  ብር 5 (አምስት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 7 (ሰባት)፣

                  ለተግባርና ለትብብር ስልጠና በሰዓት ለደረጃ 1 እና 2  ብር 6 (ስድስት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 8 (ስምንት)፣

የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜ፡ ከመጋቢት 27/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 29/2015 ዓ.ም ነው፣

የመግቢያ ፈተና ከምዝገባ ብኋላ የሚገለጽ ሆኖ ለደረጃ 3 እና 4  በ 2015 ወደ ኮሌጅ የመግቢያ ነጥብ ፣ 2014 1ኛ እና 2ኛ ዙር መግቢያ ውጤት መስፈርት መሰረት ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471353598  ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይቻላል፡፡

የ COC ምዘና ማስታወቂያ

በደረጃ 1 ፣ በደረጃ 2 እና ደረጃ 3 ከቀን 22/05/2015 እስከ 26/05/2015 ዓ.ም ድረስCOC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን በ 15/07/2015 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባን፡፡