Student Announcement

ቀን:  11/02/2018 ዓ.ም

ማስታወቂያ

 

2017 ባች ቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች በሙሉ

የ 2018 ትምህርት ዘመን ምዝገባ  የሚጀምረው 17/02/2018 ዓ.ም እስከ 19/02/2018 ዓ.ም ሲሆን ስልጠና የሚጀምረው 22/02/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በሰዓቱ እድትገኙ እናሳስባለን ።

 

ማሳሰቢያ፡ ደረጃ 1 ክፍያ ያላጠናቀቀ እና ደረጃ 1 ያልበቃ (NYC የሆነ) መመዝገብ አይችልም።

ከ 21/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ COC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን 30/12/2017 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እንድሁም በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ እና መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ለሰርትፊኬት ፎቶ ያልሰጣችሁ በእለቱ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባን፡፡

ቀን:  17/11/2017 ዓ.ም

 

የ COC ምዘና ማስታወቂያ 

ደረጃ 3(III) እና ደረጃ 4(IV) በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ ደረጃ በደረጃ COC እንድሁም ደረጃ 4 እና ደረጃ 2 holistic ምዘና ሎግ ቡክ መሙላት የምትፈልጉ በሙሉ ከ 21/11/2017 ዓ.ም እስከ 25/11/2017 ዓ.ም ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ሎግ ቡክ እንድትሞሉ (እንድትመዘገቡ) እያሳወቅን በኮሌጁ አካውንት ቁጥር 1000066466519 አራት መቶ ሃምሳ (450) ብር ገቢ እንድታደርጉ እየጠየቅን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣ ምዝገባ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

የ COC ምዘና ማስታወቂያ 

ከ 08/07/2017 ዓ.ም እስከ 12/07/2017 ዓ.ም ድረስ COC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን 26/07/2017 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ እና መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እያሳወቅን ለሰርትፊኬት ፎቶ ያልሰጣችሁ በእለቱ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባን፡፡

ደረጃ 3(III) እና ደረጃ 4(IV) በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ ደረጃ በደረጃ COC እንድሁም ደረጃ 4 holistic ምዘና ሎግ ቡክ መሙላት የምትፈልጉ በሙሉ ከ 08/07/2017 ዓ.ም እስከ 12/07/2017 ዓ.ም ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ሎግ ቡክ እንድትሞሉ (እንድትመዘገቡ) እያሳወቅን በኮሌጁ አካውንት ቁጥር 1000066466519 አራት መቶ ሃምሳ (450) ብር ገቢ እንድታደርጉ እየጠየቅን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣ ምዝገባ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

ማስታወቂያ

ለ 2015 ባች ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የ 2016 የትምህት መርሀ ግብር የመግቢያ ጊዜ ከህዳር 29 - 30/2016 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባ ቀን ከ 01/04/2016 እስከ 03/04/2016 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

 

 

 

 የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

የ COC ምዘና ማስታወቂያ

 

ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ከ ቀን 07/01/2016 ዓ.ም እስከ 11/01/2016 ዓ.ም ድረስ COC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን ጥቅምት 23/02/2016 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ እና መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባን፡፡

የ COC ምዘና ማስታወቂያ

በደረጃ 1(I), ደረጃ 2(II), ደረጃ 3(III) እና ደረጃ 4(IV) በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ COC ምዘና ሎግ ቡክ መሙላት የምትፈልጉ በሙሉ ከ መስከረም 07/01/2016 ዓ.ም እስከ 11/01/2016 ዓ.ም ብቻ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ሎግ ቡክ እንድትሞሉ

የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በ 2015 ዓ.ም አድስ ሰልጣኞች ደረጃ 1(I) እና ደረጃ 4(IV) ተቀብሎ በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር ይፈልጋል።

በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አድስ ተመዝጋቢዎች እንድሁም የ 2011 ባች ነባር ተማሪዎች የመመዝገቢያ እና የትምህርት ክፍያ ከታች በቀረበው ሰንጠረዝ መሰረት በኮሌጁ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000066466519 በመክፈልና የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከቀን 03/11/2015 እስከ 07/11/2015 ዓ.ም ኮሌጁ ሬጅስትራር በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፀን አድስ መመዝገብ የምትፈልጉ የመቁረጫ ነጥብ በ 2015 ዓ.ም ወደ ቴ/ሙ/ስ/ተቋማት የመግቢያ ውጤት፣ የ 2014 1ኛና 2ኛ ዙር ተፈታኞች ውጤት መሠረት መሆኑን አውቃችሁ መመዝገብ የምትችሉ ሙሆኑን እንገልፃለን።

ተ/ቁ

የትምህርት ክፍል

የ ክፍያ ሁኔታ

አድስ ተመዝጋቢዎች

ነባር ተማሪዎች

1

እጽዋት ሳይንስ

3386 ብር

2570 ብር

2

ተፈጥሮ ሀብት

3026 ብር

2450 ብር

3

እንስሳት ሳይንስ

3318 ብር

1730 ብር

ማሳሰቢያ፥ አድስ መመዝገብ የምትፈልጉ ተማሪዎች ትምህርት ለማስጀመር የመረጣችሁት ትምህርት ክፍል ከሚያስፈልገው ዝቅተኛ ቁጥር በታች ከሆነ 2ኛ ወይም 3ኛ ምርጫችሁ ይጠበቃል። በሦስቱም ትምህርት ክፍል በቂ ተማሪ ካልተሟላ ያስገባችሁት ብር ተመላሽ ይደረጋል።