የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በ 2015 ዓ.ም አድስ ሰልጣኞች ደረጃ 1(I) እና ደረጃ 4(IV) ተቀብሎ በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር ይፈልጋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አድስ ተመዝጋቢዎች እንድሁም የ 2011 ባች ነባር ተማሪዎች የመመዝገቢያ እና የትምህርት ክፍያ ከታች በቀረበው ሰንጠረዝ መሰረት በኮሌጁ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000066466519 በመክፈልና የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከቀን 03/11/2015 እስከ 07/11/2015 ዓ.ም ኮሌጁ ሬጅስትራር በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፀን አድስ መመዝገብ የምትፈልጉ የመቁረጫ ነጥብ በ 2015 ዓ.ም ወደ ቴ/ሙ/ስ/ተቋማት የመግቢያ ውጤት፣ የ 2014 1ኛና 2ኛ ዙር ተፈታኞች ውጤት መሠረት መሆኑን አውቃችሁ መመዝገብ የምትችሉ ሙሆኑን እንገልፃለን።
|
ተ/ቁ
|
የትምህርት ክፍል
|
የ ክፍያ ሁኔታ
|
|
አድስ ተመዝጋቢዎች
|
ነባር ተማሪዎች
|
|
1
|
እጽዋት ሳይንስ
|
3386 ብር
|
2570 ብር
|
|
2
|
ተፈጥሮ ሀብት
|
3026 ብር
|
2450 ብር
|
|
3
|
እንስሳት ሳይንስ
|
3318 ብር
|
1730 ብር
|
ማሳሰቢያ፥ አድስ መመዝገብ የምትፈልጉ ተማሪዎች ትምህርት ለማስጀመር የመረጣችሁት ትምህርት ክፍል ከሚያስፈልገው ዝቅተኛ ቁጥር በታች ከሆነ 2ኛ ወይም 3ኛ ምርጫችሁ ይጠበቃል። በሦስቱም ትምህርት ክፍል በቂ ተማሪ ካልተሟላ ያስገባችሁት ብር ተመላሽ ይደረጋል።